Idioms: people and relationships
ፈሊጣዊ አነጋገሮች፦ ሰዎችና ግንኙነቶች
Ten advanced idioms about getting on, falling out and making peace: with colleagues, family and friends.
Printable worksheetHow it works
Many English idioms describe how people treat each other. When two old rivals "bury the hatchet", nobody digs a hole: they simply stop arguing and make peace.
ብዙ የእንግሊዝኛ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ሰዎች እርስ በርስ እንዴት እንደሚተያዩ ይገልጻሉ። ሁለት የቆዩ ተቀናቃኞች "bury the hatchet" ሲሉ ማንም ጉድጓድ አይቆፍርም፤ ጠባቸውን ትተው ይታረቃሉ ማለት ነው።
Idioms like "a chip on your shoulder" or "a wolf in sheep's clothing" judge a person strongly. Saying them about someone to their face can sound rude.
እንደ "a chip on your shoulder" ወይም "a wolf in sheep's clothing" ያሉ ፈሊጦች ሰውን አጥብቀው ይፈርጃሉ። ለሰውየው ፊት ለፊት መናገር ብልግና ሊመስል ይችላል።
Words
Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.
bury the hatchetidiom
ጠብን ትቶ መታረቅ
After years of not speaking, the two brothers finally buried the hatchet at their father's birthday.
ሁለቱ ወንድማማቾች ለዓመታት ሳይነጋገሩ ከቆዩ በኋላ በአባታቸው ልደት ላይ በመጨረሻ ታረቁ።
ቃል በቃል፦ "መጥረቢያውን መቅበር"። ከረጅም ጠብ በኋላ ስለሚደረግ እርቅ ይነገራል።
give someone the cold shoulderidiom
አንድን ሰው ሆን ብሎ ችላ ማለት፣ ፊት መንሳት
Ever since I forgot her wedding, Meron has been giving me the cold shoulder.
ሠርጓን ከረሳሁበት ጊዜ ጀምሮ ሜሮን ፊት ነስታኛለች።
ቃል በቃል፦ "ለአንድ ሰው ቀዝቃዛ ትከሻ መስጠት"። ቅሬታን በዝምታ ማሳየት ነው።
በቀድሞ በደል ምክንያት የቆየ ቂምና በቀላሉ የመቀየም ባሕርይ
He has a chip on his shoulder because he never went to university.
ዩኒቨርሲቲ ስላልገባ የቆየ ቅሬታ አለበት፤ በትንሽ ነገር ይቀየማል።
ቃል በቃል፦ "በትከሻ ላይ ያለ ስንጣሪ እንጨት"። ብዙ ጊዜ በ"have" ይመጣል፦ "He has a chip on his shoulder."
bite your tongueidiom
ለመናገር እየፈለጉ ራስን ገትቶ ዝም ማለት
I wanted to tell my boss he was wrong, but I bit my tongue.
አለቃዬ እንደተሳሳተ ልነግረው ፈልጌ ነበር፤ ግን ራሴን ገትቼ ዝም አልኩ።
ቃል በቃል፦ "ምላስን መንከስ"። ጠብ ላለመፍጠር ሲባል ዝም ማለትን ያሳያል።
rub someone up the wrong wayidiom
አንድን ሰው ሳያስቡት ማበሳጨት፣ አለመጣጣም
The new supervisor rubs everyone up the wrong way with his comments.
አዲሱ ተቆጣጣሪ በአስተያየቶቹ ሁሉንም ያበሳጫል።
ቃል በቃል፦ "አንድን ሰው በተሳሳተ አቅጣጫ ማሸት"። እንደ ድመት ፀጉር በተቃራኒው ሲታሸ ያለውን ያስታውሳል። የብሪታንያ አገላለጽ ነው።
a wolf in sheep's clothingidiom
ደግና ጉዳት የሌለው መስሎ የሚታይ ግን አደገኛ ሰው
The friendly investor turned out to be a wolf in sheep's clothing.
ደግ የሚመስለው ባለሀብት በውስጡ አታላይ ሆኖ ተገኘ።
ቃል በቃል፦ "የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ"። ከመጽሐፍ ቅዱስ የመጣ ነው (ማቴዎስ 7፡15)።
on thin iceidiom
በአደገኛ ሁኔታ ላይ መሆን፣ አንድ ስሕተት ቢጨመር ችግር ውስጥ የሚገባ
After arriving late three times this week, you're on thin ice.
በዚህ ሳምንት ሦስት ጊዜ ስለዘገየህ አሁን በአደገኛ ሁኔታ ላይ ነህ።
ቃል በቃል፦ "በስስ በረዶ ላይ"። ብዙ ጊዜ በ"be" ወይም "skate" ይመጣል፦ "You're on thin ice."
ያለፈና የበረደ ችግርን ቆስቁሶ አለማንሳት
I thought about asking him about the old argument, but decided to let sleeping dogs lie.
ስለ ድሮው ጠብ ልጠይቀው አስቤ ነበር፤ ግን ያለፈውን ላለመቆስቆስ ወሰንኩ።
ቃል በቃል፦ "የተኙ ውሾችን ተኝተው እንዲቆዩ መተው"። እንደ ምክር ይነገራል።
burn your bridgesidiom
ወደ ኋላ መመለስ በማይቻልበት ሁኔታ ግንኙነትን ማበላሸት
Be polite when you resign. You don't want to burn your bridges.
ሥራ ስትለቅ በትሕትና ይሁን፤ ግንኙነትህን ማበላሸት አትፈልግም።
ቃል በቃል፦ "ድልድዮችህን ማቃጠል"። ብዙ ጊዜ ሥራ ሲለቁ ስለሚሰጥ ምክር ይነገራል።
keep someone at arm's lengthidiom
ከአንድ ሰው ጋር በጣም ላለመቀራረብ ርቀትን መጠበቅ
She's polite to her new neighbours, but she keeps them at arm's length.
ለአዲሶቹ ጎረቤቶቿ ትሑት ናት፤ ግን ብዙም አትቀራረባቸውም።
ቃል በቃል፦ "አንድን ሰው በክንድ ርዝመት ማራቅ"። ጥንቃቄን ወይም አለመተማመንን ያሳያል።
