Skip to content
VocabularyB1 · Intermediate

Idioms: time and money

ፈሊጣዊ አነጋገሮች፦ ጊዜና ገንዘብ

Ten everyday idioms about time and money: being just in time, saving, and paying the bills.

Printable worksheet

How it works

An idiom is a group of words whose meaning is different from the meaning of each word. "We arrived in the nick of time" has nothing to do with a cut (a nick): it means "We arrived just before it was too late".

ፈሊጣዊ አነጋገር (idiom) ትርጉሙ ከእያንዳንዱ ቃል ትርጉም የተለየ የሆነ የቃላት ስብስብ ነው። "We arrived in the nick of time" ከመቆረጥ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ "ጊዜው ሳያልፍ ልክ በሰዓቱ ደረስን" ማለት ነው።

Learn each idiom as one block, together with its example sentence. Don't translate it word by word.

እያንዳንዱን ፈሊጥ እንደ አንድ ሙሉ ቁራጭ ከምሳሌ ዓረፍተ ነገሩ ጋር ይማሩት። ቃል በቃል አይተርጉሙት።

Idioms are informal. Use them when you talk with friends, not in a formal letter or an exam essay.

ፈሊጣዊ አነጋገሮች መደበኛ አይደሉም። ከጓደኞች ጋር ሲያወሩ ይጠቀሙባቸው፤ በመደበኛ ደብዳቤ ወይም በፈተና ድርሰት ውስጥ አይጠቀሙባቸው።

Words

Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.

  • in the nick of timeidiom

    ልክ በመጨረሻው ሰዓት፣ ጊዜው ሳያልፍ

    We reached the bus station in the nick of time. The bus to Bahir Dar was just leaving.

    ልክ በመጨረሻው ሰዓት አውቶቡስ ተራ ደረስን። ወደ ባሕር ዳር የሚሄደው አውቶቡስ ሊነሳ ነበር።

    ቃል በቃል፦ "በጊዜው ጫፍ ላይ"። ሊዘገዩ ሲሉ ልክ በሰዓቱ መድረስን ይገልጻል።

  • save for a rainy dayidiom

    ለክፉ ቀን ገንዘብ መቆጠብ

    My mother always tells me to save some of my salary for a rainy day.

    እናቴ ከደመወዜ ጥቂቱን ለክፉ ቀን እንድቆጥብ ሁልጊዜ ትነግረኛለች።

    ቃል በቃል፦ "ለዝናባማ ቀን መቆጠብ"። ለወደፊት ችግር ወይም ድንገተኛ ወጪ ገንዘብ ማስቀመጥ።

  • make ends meetidiom

    ባለው ገንዘብ ኑሮን መምራት፣ ወጪን መሸፈን

    Prices are going up, so many families find it hard to make ends meet.

    ዋጋ እየጨመረ ስለሆነ ብዙ ቤተሰቦች ኑሯቸውን መምራት ከብዷቸዋል።

    ቃል በቃል፦ "ጫፎችን ማገናኘት"። ገቢው ለወጪው በጭንቅ ሲበቃ ይነገራል።

  • time is moneyidiom

    ጊዜ ውድ ነው፤ ጊዜን ማባከን ገንዘብን እንደማባከን ነው

    Let's start the meeting now. Time is money!

    ስብሰባውን አሁን እንጀምር። ጊዜ ውድ ነው!

    ቃል በቃል፦ "ጊዜ ገንዘብ ነው"። ሰዎች እንዲፈጥኑ ለማሳሰብ ይነገራል።

  • in the long runidiom

    ውሎ አድሮ፣ በረጅም ጊዜ

    Learning English takes time, but in the long run it will help you get a better job.

    እንግሊዝኛ መማር ጊዜ ይወስዳል፤ ውሎ አድሮ ግን የተሻለ ሥራ እንድታገኝ ይረዳሃል።

    ቃል በቃል፦ "በረጅሙ ሩጫ"። ስለ ሩቅ ወደፊት ውጤት ሲነገር።

  • at the drop of a hatidiom

    ወዲያውኑ፣ ሳያመነቱ

    My friend Dawit will help you at the drop of a hat. Just call him.

    ጓደኛዬ ዳዊት ወዲያውኑ ይረዳሃል። በቃ ደውልለት።

    ቃል በቃል፦ "ኮፍያ ሲወድቅ"። ምንም ሳያስቡ ወይም ሳይዘገዩ ወዲያው ማድረግ።

  • from time to timeidiom

    አልፎ አልፎ፣ አንዳንድ ጊዜ

    I don't eat out often, but from time to time I go to a restaurant with my family.

    ብዙ ጊዜ ውጭ አልበላም፤ አልፎ አልፎ ግን ከቤተሰቤ ጋር ምግብ ቤት እሄዳለሁ።

    ቃል በቃል፦ "ከጊዜ ወደ ጊዜ"። በአማርኛ "ከጊዜ ወደ ጊዜ" "እየጨመረ" ማለት ሊሆን ይችላል፤ በእንግሊዝኛ ግን "አልፎ አልፎ" ማለት ነው።

  • kill timeidiom

    ጊዜ ማሳለፍ (ሲጠብቁ)

    Our flight was late, so we killed time by drinking coffee at the airport.

    በረራችን ስለዘገየ አውሮፕላን ማረፊያው ቡና እየጠጣን ጊዜ አሳለፍን።

    ቃል በቃል፦ "ጊዜን መግደል"። አንድ ነገር ሲጠብቁ ጊዜው እንዲያልፍ ሌላ ነገር ማድረግ።

  • money doesn't grow on treesidiom

    ገንዘብ በቀላሉ አይገኝም፤ በጥንቃቄ አውጣ

    "Can I have a new phone?" "No. Money doesn't grow on trees, you know!"

    "አዲስ ስልክ ልታገዛልኝ ትችላለህ?" "አይሆንም። ገንዘብ በቀላሉ አይገኝም!"

    ቃል በቃል፦ "ገንዘብ በዛፍ ላይ አይበቅልም"። ብዙ ጊዜ ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሉት ነው።

  • on the dotidiom

    ልክ በሰዓቱ፣ በትክክለኛው ሰዓት

    The class starts at nine o'clock on the dot, so please don't be late.

    ትምህርቱ ልክ ሦስት ሰዓት ላይ ይጀምራል፤ ስለዚህ እባካችሁ አትዘግዩ።

    ቃል በቃል፦ "በነጥቡ ላይ"። ከሰዓት በኋላ ይመጣል፦ "at nine o'clock on the dot"።

Practice· ልምምድ

Question 1 of 8
Selam arrived in the nick of time. When did she arrive?

ሰላም "in the nick of time" ደረሰች። መቼ ደረሰች?