Skip to content
VocabularyA2 · Elementary

Words: sports and free time

ቃላት፦ ስፖርትና የትርፍ ጊዜ

Fifteen words for sport and free time: team, coach, referee, score, medal, hobby, chess, hiking and more.

Printable worksheet

How it works

Ethiopians love football and running. Use these words to talk about a match on TV, your favourite athlete or what you do at the weekend.

ኢትዮጵያውያን እግር ኳስንና ሩጫን ይወዳሉ። በቴሌቪዥን ስለሚታይ ጨዋታ፣ ስለሚወዱት አትሌት ወይም ቅዳሜና እሁድ ስለሚያደርጉት ነገር ለመናገር እነዚህን ቃላት ይጠቀሙ።

We say "play football" and "play chess", but "go hiking" and "go swimming". Activities that end in -ing usually take "go".

"play football" እና "play chess" እንላለን፤ ግን "go hiking" እና "go swimming" እንላለን። በ-ing የሚጨርሱ እንቅስቃሴዎች ብዙ ጊዜ ከ"go" ጋር ይመጣሉ።

Words

Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.

  • teamnoun

    ቡድን

    My brother plays for the school football team.

    ወንድሜ ለትምህርት ቤቱ የእግር ኳስ ቡድን ይጫወታል።

    አብረው የሚጫወቱ ወይም የሚሠሩ ሰዎች። "a football team" = የእግር ኳስ ቡድን።

  • playernoun

    ተጫዋች

    He is the best player in our team.

    እሱ በቡድናችን ውስጥ ምርጡ ተጫዋች ነው።

    ስፖርት ወይም ጨዋታ የሚጫወት ሰው። ከ"play" (መጫወት) የመጣ ነው።

  • coachnoun

    አሠልጣኝ

    Our coach tells us to drink water during training.

    አሠልጣኛችን በልምምድ ጊዜ ውሃ እንድንጠጣ ይነግረናል።

    ቡድንን ወይም አትሌትን የሚያሠለጥን ሰው። እንደ ግስም ይመጣል፦ "He coaches runners." (ሯጮችን ያሠለጥናል)።

  • refereenoun

    ዳኛ (የጨዋታ)

    The referee showed him a yellow card.

    ዳኛው ቢጫ ካርድ አሳየው።

    በእግር ኳስና በሌሎች ጨዋታዎች ሕጉን የሚያስከብር ሰው። አጠራሩ፦ "re-fuh-REE"፤ ጭነቱ በመጨረሻው ክፍል ላይ ነው።

  • scorenoun

    ውጤት፤ ጎል ማግባት

    What was the score at half-time?

    በእረፍት ሰዓት ውጤቱ ስንት ነበር?

    እንደ ስም "ውጤት" ነው፦ "The score is 2–1."። እንደ ግስ "ጎል ወይም ነጥብ ማግኘት" ነው፦ "She scored a goal."።

  • goalnoun

    ጎል፤ ግብ

    Dawit scored two goals in the last ten minutes.

    ዳዊት በመጨረሻዎቹ አሥር ደቂቃዎች ሁለት ጎሎች አገባ።

    በእግር ኳስ "ጎል" ማለት ነው፦ "score a goal"። በሌላ ትርጉም "ዓላማ፣ ግብ" ማለት ነው፦ "My goal is to pass the exam."።

  • racenoun

    ውድድር (የሩጫ)

    Thousands of people run the big race in Addis Ababa every year.

    በየዓመቱ በአዲስ አበባ በሚደረገው ትልቅ የሩጫ ውድድር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይሮጣሉ።

    ማን ፈጣን እንደሆነ የሚታይበት ውድድር። "run a race" = ውድድር መሮጥ፤ "win a race" = ውድድር ማሸነፍ።

  • stadiumnoun

    ስታዲየም

    The stadium was full for the final match.

    ለፍጻሜው ጨዋታ ስታዲየሙ ሞልቶ ነበር።

    ትልቅ የስፖርት ሜዳ ከተመልካቾች መቀመጫ ጋር። አጠራሩ፦ "STAY-dee-um"።

  • medalnoun

    ሜዳሊያ

    She won a gold medal in the 5,000 metres.

    በ5,000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈች።

    ለአሸናፊዎች የሚሰጥ ክብ ብረት፦ "gold medal" (የወርቅ)፣ "silver medal" (የብር)፣ "bronze medal" (የነሐስ)።

  • prizenoun

    ሽልማት

    The first prize is a new bicycle.

    የመጀመሪያው ሽልማት አዲስ ብስክሌት ነው።

    ለአሸናፊ የሚሰጥ ነገር ወይም ገንዘብ። "win a prize" = ሽልማት ማሸነፍ። "price" (ዋጋ) ከሚለው ጋር አያምታቱት።

  • fannoun

    ደጋፊ፤ አድናቂ

    The fans sang and danced after the match.

    ደጋፊዎቹ ከጨዋታው በኋላ ዘፈኑ፤ ጨፈሩም።

    አንድን ቡድን፣ ተጫዋች ወይም ዘፋኝ በጣም የሚወድ ሰው። በሌላ ትርጉም "ማራገቢያ" ማለት ነው።

  • hobbynoun

    የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ

    Her hobby is taking photos of birds.

    የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዋ የወፎችን ፎቶ ማንሳት ነው።

    በትርፍ ጊዜ ለደስታ የሚያደርጉት ነገር። ብዙ ቁጥሩ "hobbies" ነው። "What are your hobbies?" የተለመደ ጥያቄ ነው።

  • chessnoun

    ቼዝ፣ ሰንጠረዥ

    My grandfather taught me to play chess.

    አያቴ ቼዝ መጫወት አስተማረኝ።

    በሁለት ሰዎች በሰሌዳ ላይ የሚጫወት የአእምሮ ጨዋታ። "play chess" ይባላል፤ "a" ወይም "the" አያስፈልገውም።

  • hikingnoun

    የእግር ጉዞ (በተራራ ወይም በገጠር)

    We went hiking on Mount Entoto last Sunday.

    ባለፈው እሁድ እንጦጦ ተራራ ላይ የእግር ጉዞ አደረግን።

    ለደስታና ለጤና በተራራ ወይም በገጠር ረጅም መንገድ በእግር መሄድ። "go hiking" ይባላል።

  • practiseverb

    መለማመድ

    The runners practise every morning at six.

    ሯጮቹ በየቀኑ ጠዋት በአሥራ ሁለት ሰዓት ይለማመዳሉ።

    በደንብ ለመቻል አንድን ነገር ደጋግሞ መሥራት። በብሪታንያ እንግሊዝኛ ግሱ "practise"፣ ስሙ "practice" ነው፤ አሜሪካውያን ሁለቱንም "practice" ብለው ይጽፋሉ።

Practice· ልምምድ

Question 1 of 8
The person who makes sure players follow the rules is the …

ተጫዋቾች ሕጉን እንዲከተሉ የሚያደርገው ሰው … ነው።