Words: research and higher education
ቃላት፦ ምርምርና ከፍተኛ ትምህርት
Fifteen words for university study and research: thesis, supervisor, scholarship, methodology, plagiarism, findings and more.
Printable worksheetHow it works
Whether you are writing a senior essay, applying for a master's programme or reading journal articles, these words come up again and again. They are also useful for IELTS Academic reading passages.
የመመረቂያ ጽሑፍ እየጻፉ፣ ለማስተርስ ፕሮግራም እያመለከቱ ወይም የምርምር መጽሔት ጽሑፎችን እያነበቡ ቢሆን እነዚህ ቃላት ደጋግመው ይመጣሉ። ለIELTS Academic የንባብ ምንባቦችም ጠቃሚ ናቸው።
"Data" and "findings" usually take a plural verb in academic writing: "The data show …", "The findings suggest …". "Curriculum" has the plural "curricula".
በአካዳሚክ ጽሑፍ "data" እና "findings" ብዙ ጊዜ የብዙ ቁጥር ግስ ይወስዳሉ፦ "The data show …"፣ "The findings suggest …"። የ"curriculum" ብዙ ቁጥር "curricula" ነው።
Words
Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.
thesisnoun
የመመረቂያ ጽሑፍ
Dawit is writing his master's thesis on water use in small farms.
ዳዊት የማስተርስ መመረቂያ ጽሑፉን በአነስተኛ እርሻዎች ስለሚደረግ የውኃ አጠቃቀም እየጻፈ ነው።
ለዲግሪ የሚጻፍ ረጅም የምርምር ጽሑፍ። ብዙ ቁጥሩ "theses" (THEE-seez) ነው። "write / submit / defend a thesis" ይባላል።
supervisornoun
አማካሪ፣ ተቆጣጣሪ መምህር
My supervisor asked me to rewrite the introduction.
አማካሪዬ መግቢያውን እንደገና እንድጽፍ ጠየቁኝ።
የተማሪን ምርምር የሚመራና የሚመክር መምህር። በሥራ ቦታ ደግሞ "ተቆጣጣሪ፣ አለቃ" ማለት ነው። ግሱ "supervise" ነው።
scholarshipnoun
የትምህርት ዕድል፣ ስኮላርሺፕ
Selam won a scholarship to study engineering abroad.
ሰላም በውጭ አገር ምሕንድስና ለመማር የትምህርት ዕድል አገኘች።
የትምህርት ክፍያን የሚሸፍን ድጋፍ። "apply for / win / be awarded a scholarship" ይባላል።
undergraduatenoun
የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ
As an undergraduate, she studied economics at Addis Ababa University.
የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ሳለች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢኮኖሚክስ ተምራለች።
የመጀመሪያ ዲግሪውን የሚማር ተማሪ። ዲግሪ ካገኘ በኋላ የሚማር "postgraduate" ወይም "graduate student" ይባላል።
graduateverb
መመረቅ
Yonas graduated from Bahir Dar University last July.
ዮናስ ባለፈው ሐምሌ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመረቀ።
ትምህርትን ጨርሶ ዲግሪ ማግኘት። "graduate from a university" ይባላል። እንደ ስም ("a graduate" = ተመራቂ) ሲሆን የመጨረሻው ክፍል "-gət" ይነበባል፤ እንደ ግስ "-gate"።
tuition feenoun
የትምህርት ክፍያ
Private colleges charge higher tuition fees than public universities.
የግል ኮሌጆች ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የበለጠ የትምህርት ክፍያ ያስከፍላሉ።
ለትምህርት የሚከፈል ገንዘብ። ብዙ ጊዜ በብዙ ቁጥር ይመጣል፦ "tuition fees"። "tuition" ብቻውን "ማስጠናት" ማለትም ሊሆን ይችላል።
lecturenoun
ሌክቸር፣ ገለጻ
The lecture starts at eight, so don't be late.
ሌክቸሩ በሁለት ሰዓት ይጀምራል፤ ስለዚህ አትዘግዩ።
በዩኒቨርሲቲ መምህር ለብዙ ተማሪዎች የሚሰጠው ትምህርት። "give / attend a lecture" ይባላል። መምህሩ "lecturer" ነው።
plagiarismnoun
የሌላውን ሥራ እንደራስ ማቅረብ
Copying from a website without citing it is plagiarism.
ምንጩን ሳይጠቅሱ ከድረ ገጽ መገልበጥ የሌላውን ሥራ እንደራስ ማቅረብ ነው።
የሌላ ሰውን ጽሑፍ ወይም ሐሳብ ምንጩን ሳይጠቅሱ እንደራስ ማቅረብ። "PLAY-juh-riz-um" ተብሎ ይነበባል። ግሱ "plagiarise" ነው።
methodologynoun
የአጠናን ዘዴ
In the methodology chapter, explain how you chose the people in your study.
በአጠናን ዘዴው ምዕራፍ በጥናትዎ ውስጥ የተካተቱትን ሰዎች እንዴት እንደመረጡ ያስረዱ።
ምርምሩ እንዴት እንደተሠራ የሚያስረዳ ክፍል፦ መረጃ እንዴት እንደተሰበሰበና እንደተተነተነ። በመመረቂያ ጽሑፍ ውስጥ የራሱ ምዕራፍ አለው።
questionnairenoun
መጠይቅ
Two hundred students completed the questionnaire.
ሁለት መቶ ተማሪዎች መጠይቁን ሞሉ።
መረጃ ለመሰብሰብ የሚዘጋጅ የጽሑፍ ጥያቄዎች ዝርዝር። "kwes-chuh-NAIR" ተብሎ ይነበባል። "fill in / complete a questionnaire" ይባላል።
datanoun
መረጃ፣ ዳታ
She spent three months collecting data in rural health centres.
በገጠር ጤና ጣቢያዎች መረጃ በመሰብሰብ ሦስት ወር አሳለፈች።
ለምርምር የሚሰበሰቡ ቁጥሮችና እውነታዎች። "collect / analyse data" ይባላል። በአካዳሚክ ጽሑፍ ብዙ ጊዜ እንደ ብዙ ቁጥር ይቆጠራል፦ "the data show"።
findingsnoun
ግኝቶች
The findings suggest that students learn better in smaller classes.
ግኝቶቹ ተማሪዎች በትናንሽ ክፍሎች በተሻለ እንደሚማሩ ይጠቁማሉ።
ጥናቱ ያገኛቸው ውጤቶች። ሁልጊዜ በብዙ ቁጥር ይመጣል። "The findings suggest / show …" ይባላል።
peer reviewnoun
የአቻ ግምገማ
Her article was accepted after peer review.
ጽሑፏ የአቻ ግምገማ ካለፈ በኋላ ተቀባይነት አገኘ።
አንድ ጽሑፍ ከመታተሙ በፊት በዘርፉ ባሉ ሌሎች ባለሙያዎች መገምገሙ። "a peer-reviewed journal" = በአቻ የሚገመገም መጽሔት።
citationnoun
ዋቢ፣ የምንጭ ጥቅስ
Every quotation in your essay needs a citation.
በድርሰትዎ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ጥቅስ ዋቢ ያስፈልገዋል።
የተጠቀሙበትን ምንጭ በጽሑፍዎ ውስጥ መጥቀስ። ግሱ "cite" ነው ("site" እና "sight" ከሚሉት ጋር ድምፁ አንድ ነው)።
curriculumnoun
ሥርዓተ ትምህርት
The new curriculum gives more time to practical skills.
አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ለተግባራዊ ክህሎቶች የበለጠ ጊዜ ይሰጣል።
በአንድ ትምህርት ቤት ወይም ፕሮግራም የሚሰጡ ትምህርቶች በሙሉ። ብዙ ቁጥሩ "curricula" ነው። "the new curriculum" = አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት።
