Skip to content
VocabularyA2 · Elementary

Words: home and family

ቃላት፦ ቤትና ቤተሰብ

Fifteen words for the parts of a house, furniture and the people in your family.

Printable worksheet

How it works

With these words you can describe your home and talk about your family: "Our house has three bedrooms. I live with my parents, my sister and my grandmother."

በእነዚህ ቃላት ቤትዎን መግለጽና ስለ ቤተሰብዎ መናገር ይችላሉ፦ "Our house has three bedrooms. I live with my parents, my sister and my grandmother." (ቤታችን ሦስት መኝታ ቤቶች አሉት። ከወላጆቼ፣ ከእህቴና ከአያቴ ጋር እኖራለሁ።)

English has one word, "cousin", for the child of any aunt or uncle, boy or girl. Amharic says more: የአጎት ልጅ or የአክስት ልጅ.

እንግሊዝኛ ለአጎትም ሆነ ለአክስት ልጅ፣ ወንድም ሆነ ሴት አንድ ቃል ብቻ አለው፦ "cousin"። አማርኛ ግን በዝርዝር ይናገራል፦ የአጎት ልጅ ወይም የአክስት ልጅ።

Words

Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.

  • housenoun

    ቤት

    Their house is near the church.

    ቤታቸው ቤተ ክርስቲያኑ አጠገብ ነው።

    "house" ሕንፃውን ያመለክታል፤ "home" ደግሞ የምንኖርበትን ቦታ (ስሜትን ጨምሮ)።

  • bedroomnoun

    መኝታ ቤት

    I share a bedroom with my brother.

    ከወንድሜ ጋር አንድ መኝታ ቤት እጋራለሁ።

    bed (አልጋ) + room (ክፍል)። ሳሎን ደግሞ "living room" ነው።

  • doornoun

    በር

    Please close the door. It's cold.

    እባክህ በሩን ዝጋው። ቀዝቃዛ ነው።

    "open the door" = በሩን መክፈት፤ "close the door" = በሩን መዝጋት።

  • windownoun

    መስኮት

    Open the window. The room is hot.

    መስኮቱን ክፈተው። ክፍሉ ሞቃት ነው።

    ብዙ ቁጥር፦ windows።

  • roofnoun

    ጣሪያ

    In the rainy season, the rain is loud on the roof.

    በክረምት ዝናቡ ጣሪያው ላይ ይጮኻል።

    የቤቱ የውጭ ክዳን። የክፍሉ ውስጠኛ ጣሪያ "ceiling" ይባላል።

  • bednoun

    አልጋ

    I go to bed at ten o'clock.

    ከምሽቱ አራት ሰዓት እተኛለሁ።

    "go to bed" = ለመተኛት መሄድ ("the" አያስፈልግም)።

  • chairnoun

    ወንበር

    There are six chairs around the table.

    በጠረጴዛው ዙሪያ ስድስት ወንበሮች አሉ።

    ብዙ ቁጥር፦ chairs። ረጅም የብዙ ሰው መቀመጫ "sofa" ይባላል።

  • tablenoun

    ጠረጴዛ

    Your keys are on the table.

    ቁልፎችህ ጠረጴዛው ላይ ናቸው።

    "on the table" = ጠረጴዛው ላይ። "under the table" = ከጠረጴዛው ሥር።

  • parentsnoun

    ወላጆች

    My parents live in Bahir Dar.

    ወላጆቼ ባሕር ዳር ይኖራሉ።

    እናትና አባት በአንድ ላይ። አንዱ ብቻ "a parent" (ወላጅ) ይባላል።

  • sisternoun

    እህት

    My older sister is a nurse.

    ታላቅ እህቴ ነርስ ናት።

    ታላቅ እህት = older (big) sister፤ ታናሽ እህት = younger (little) sister።

  • brothernoun

    ወንድም

    I have two brothers and one sister.

    ሁለት ወንድሞችና አንዲት እህት አሉኝ።

    ታላቅ ወንድም = older brother፤ ታናሽ ወንድም = younger brother።

  • grandmothernoun

    ሴት አያት፣ አያት

    My grandmother makes the best coffee.

    አያቴ ምርጥ ቡና ታፈላለች።

    ወንድ አያት = grandfather። በንግግር "grandma" ወይም "granny" ይባላል።

  • auntnoun

    አክስት

    My aunt lives with us.

    አክስቴ ከእኛ ጋር ትኖራለች።

    የእናት ወይም የአባት እህት። አጎት ደግሞ "uncle" ነው።

  • cousinnoun

    የአጎት ልጅ፣ የአክስት ልጅ

    My cousin and I go to the same school.

    እኔና የአጎቴ ልጅ አንድ ትምህርት ቤት እንማራለን።

    ለወንድም ለሴትም አንድ ቃል ነው። "s" እንደ "ዝ" ይነበባል፦ "ካዝን"።

  • neighbournoun

    ጎረቤት

    Our neighbours come for coffee every afternoon.

    ጎረቤቶቻችን ሁልጊዜ ከሰዓት በኋላ ለቡና ይመጣሉ።

    በአሜሪካ እንግሊዝኛ "neighbor" ተብሎ ይጻፋል። "gh" አይነበብም።

Practice· ልምምድ

Question 1 of 8
Your mother and father are your …

እናትህና አባትህ … ናቸው።