Skip to content
VocabularyB2 · Upper intermediate

Words: feelings and character

ቃላት፦ ስሜትና ጠባይ

Fifteen adjectives to describe how people feel and what they are like, from generous and humble to stubborn and selfish.

Printable worksheet

How it works

Some adjectives describe a feeling that comes and goes (anxious, embarrassed, frustrated). Others describe a person's character, which stays the same (generous, stubborn, reliable). You need both to describe people in a conversation, a job reference or an essay.

አንዳንድ ቅጽሎች መጥቶ የሚሄድ ስሜትን ይገልጻሉ (anxious, embarrassed, frustrated)። ሌሎች ደግሞ የማይለወጥ የሰውን ጠባይ ይገልጻሉ (generous, stubborn, reliable)። በንግግር፣ በሥራ ምስክርነት ደብዳቤ ወይም በድርሰት ሰዎችን ለመግለጽ ሁለቱም ያስፈልጉዎታል።

Learn the preposition with the adjective: "grateful for" something, "jealous of" someone, "anxious about" an exam, "patient with" children.

ቅጽሉን ከመስተዋድዱ ጋር ይማሩ፦ ለአንድ ነገር "grateful for"፣ በአንድ ሰው "jealous of"፣ ስለ ፈተና "anxious about"፣ ከልጆች ጋር "patient with"።

Words

Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.

  • generousadjective

    ለጋስ፣ ቸር

    Our neighbour is very generous: she always shares her food with us during the holidays.

    ጎረቤታችን በጣም ለጋስ ናት፤ በበዓላት ሁልጊዜ ምግቧን ታካፍለናለች።

    ገንዘቡን፣ ጊዜውን ወይም ንብረቱን በደስታ ለሌሎች የሚሰጥ። ስሙ "generosity" (ልግስና) ነው።

  • stubbornadjective

    ግትር፣ እልኸኛ

    He is too stubborn to admit that he took the wrong road.

    የተሳሳተ መንገድ እንደያዘ ለማመን በጣም ግትር ነው።

    ሌሎች ቢመክሩትም ሐሳቡን የማይቀይር። አሉታዊ ትርጉም አለው።

  • anxiousadjective

    የተጨነቀ፣ የሚሰጋ

    Many students feel anxious about the national exam.

    ብዙ ተማሪዎች ስለ ብሔራዊ ፈተናው ይጨነቃሉ።

    ስለሚመጣ ነገር የሚጨነቅ። "anxious about" ይባላል። ስሙ "anxiety" (ጭንቀት) ነው።

  • gratefuladjective

    አመስጋኝ

    I am very grateful to my teachers for their support.

    መምህሮቼ ስላደረጉልኝ ድጋፍ በጣም አመስጋኝ ነኝ።

    ለተደረገለት መልካም ነገር ምስጋና የሚሰማው። "grateful for" አንድ ነገር፣ "grateful to" አንድ ሰው።

  • jealousadjective

    ቀናተኛ፣ የሚቀና

    She was jealous of her sister's new phone.

    በእህቷ አዲስ ስልክ ቀናች።

    ሌላው ያለውን ነገር የሚመኝና የሚከፋው። "jealous of" ይባላል።

  • honestadjective

    ሐቀኛ፣ እውነተኛ

    To be honest, I didn't understand the lesson.

    እውነቱን ለመናገር ትምህርቱ አልገባኝም።

    እውነት የሚናገርና የማያታልል። "h" አይነበብም፦ "onest"። ተቃራኒው "dishonest" ነው።

  • ambitiousadjective

    ትልቅ ምኞት ያለው

    Hana is ambitious: she wants to open her own company by the age of thirty.

    ሃና ትልቅ ምኞት አላት፤ በሠላሳ ዓመቷ የራሷን ድርጅት መክፈት ትፈልጋለች።

    በሕይወቱ ከፍተኛ ስኬት ለማግኘት የሚጥር። ብዙ ጊዜ አዎንታዊ ነው።

  • confidentadjective

    በራሱ የሚተማመን

    After months of practice, he felt confident speaking English in meetings.

    ከወራት ልምምድ በኋላ በስብሰባዎች እንግሊዝኛ ለመናገር በራሱ ተማመነ።

    ችሎታውን የሚያምን። ስሙ "confidence" (በራስ መተማመን) ነው።

  • shyadjective

    ዓይናፋር

    My son is shy at first, but he talks a lot once he knows you.

    ልጄ መጀመሪያ ላይ ዓይናፋር ነው፤ ካወቃችሁ በኋላ ግን ብዙ ያወራል።

    ከማያውቃቸው ሰዎች ጋር ለመናገር የሚፈራ። ተቃራኒው "outgoing" ነው።

  • patientadjective

    ታጋሽ

    A good teacher is patient with slow learners.

    ጥሩ መምህር ቀስ ብለው ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር ታጋሽ ነው።

    ሳይናደድ መጠበቅ የሚችል። ስምም ነው፦ "a patient" = በሽተኛ። ተቃራኒው "impatient" ነው።

  • selfishadjective

    ራስ ወዳድ

    It was selfish of him to eat all the bread before the others arrived.

    ሌሎቹ ሳይመጡ ዳቦውን ሁሉ መብላቱ ራስ ወዳድነት ነበር።

    ስለ ራሱ ብቻ የሚያስብ። ተቃራኒው "generous" ወይም "unselfish" ነው።

  • embarrassedadjective

    ያፈረ፣ የተሸማቀቀ

    I was embarrassed when I called my teacher "Mum" in class.

    በክፍል ውስጥ መምህሬን "እማዬ" ብዬ ስጠራት አፈርኩ።

    ስሕተት ሠርቶ በሌሎች ፊት ሲያፍር። "embarrassing" ደግሞ አሳፋሪውን ነገር ይገልጻል።

  • frustratedadjective

    የተበሳጨ

    She felt frustrated because the internet kept stopping during her online class.

    በኦንላይን ትምህርቷ ወቅት ኢንተርኔቱ እየተቋረጠ ስላስቸገራት ተበሳጨች።

    ሞክሮ ሞክሮ ሳይሳካለት ሲቀር የሚሰማው ብስጭት። "frustrating" ብስጭት የሚያመጣውን ነገር ይገልጻል።

  • reliableadjective

    አስተማማኝ፣ የሚታመን

    Dawit is very reliable: if he says he will come at eight, he comes at eight.

    ዳዊት በጣም አስተማማኝ ነው፤ በሁለት ሰዓት እመጣለሁ ካለ በሁለት ሰዓት ይመጣል።

    የገባውን ቃል የሚፈጽም፣ ሊተማመኑበት የሚችሉት ሰው ወይም ነገር። "a reliable car" ብዙ ጊዜ የማይበላሽ መኪና ነው።

  • humbleadjective

    ትሑት

    Although he is a famous runner, he is still humble and kind.

    ታዋቂ ሯጭ ቢሆንም አሁንም ትሑትና ደግ ነው።

    ስኬታማ ቢሆንም የማይኩራራ። ተቃራኒው "arrogant" (ትዕቢተኛ) ነው።

Practice· ልምምድ

Question 1 of 8
Selam never changes her mind, even when she is wrong. She is …

ሰላም ብትሳሳትም እንኳ ሐሳቧን አትቀይርም። እሷ … ናት።