Talking about your job
ስለ ሥራዎ መናገር
Say what you do, where you work and when you start.
Printable worksheetUseful phrases
Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.
I work as a …phrase
… ሆኜ እሠራለሁ።
I work as a cashier at a bank in Piassa.
ፒያሳ ባለ አንድ ባንክ ውስጥ ገንዘብ ተቀባይ ሆኜ እሠራለሁ።
ሥራዎ ምን እንደሆነ ለመናገር።
Where do you work?phrase
የት ነው የምትሠራው?
Nice to meet you, Hana. Where do you work?
ሐና፣ ስለተዋወቅን ደስ ብሎኛል። የት ነው የምትሠሪው?
የአንድን ሰው የሥራ ቦታ ለመጠየቅ፤ ቀለል ያለ ጥያቄ ነው።
I start work at …phrase
ሥራ የምገባው … ነው።
I start work at 8:30, so I leave home at seven.
ሥራ የምገባው 2:30 ላይ ነው፤ ስለዚህ ከቤት 1 ሰዓት ላይ እወጣለሁ።
ሥራ የሚጀምሩበትን ሰዓት ለመናገር።
I really like my job.phrase
ሥራዬን በጣም እወደዋለሁ።
I really like my job because I help people every day.
በየቀኑ ሰዎችን ስለምረዳ ሥራዬን በጣም እወደዋለሁ።
ስለ ሥራዎ ያለዎትን ጥሩ ስሜት ለመናገር።
I'm looking for work at the moment.phrase
አሁን ሥራ እየፈለግሁ ነው።
I finished college last year, and I'm looking for work at the moment.
ባለፈው ዓመት ኮሌጅ ጨርሻለሁ፤ አሁን ሥራ እየፈለግሁ ነው።
ሥራ እንደሌለዎትና እየፈለጉ እንደሆነ ለመናገር።
