Setting boundaries politely
ገደብን በትሕትና ማስቀመጥ
Say clearly and kindly what you are and are not willing to do.
Printable worksheetUseful phrases
Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.
I'd rather not talk about that, if you don't mind.phrase
ቅር ካላለህ ስለዚያ ባናወራ እመርጣለሁ።
My salary? I'd rather not talk about that, if you don't mind.
ደሞዜ? ቅር ካላለህ ስለዚያ ባናወራ እመርጣለሁ።
ስለ ግል ጉዳይ ሲጠየቁ መልስ ላለመስጠት በትሕትና ለመናገር።
I'd appreciate it if you didn't …phrase
… ባታደርግ ደስ ይለኛል።
I'd appreciate it if you didn't use my laptop without asking.
ሳትጠይቀኝ ላፕቶፔን ባትጠቀም ደስ ይለኛል።
አንድ ሰው የሚያደርገውን ነገር እንዲያቆም በትሕትና ግን በጥብቅ ለመጠየቅ።
I need a bit of space right now.phrase
አሁን ለብቻዬ ትንሽ ጊዜ ያስፈልገኛል።
It's nothing personal, Meron. I need a bit of space right now.
ሜሮን፣ ባንቺ ምክንያት አይደለም። አሁን ለብቻዬ ትንሽ ጊዜ ያስፈልገኛል።
ለማሰብ ወይም ለማረፍ ለብቻዎ መሆን እንደሚፈልጉ ለመናገር።
I don't answer work calls after …phrase
ከ… በኋላ የሥራ ስልክ አላነሳም።
I don't answer work calls after seven, but I'll reply first thing in the morning.
ከምሽቱ አንድ ሰዓት በኋላ የሥራ ስልክ አላነሳም፤ ግን ጠዋት ቀድሜ እመልሳለሁ።
ከሥራ ሰዓት ውጭ ያለዎትን ገደብ ለባልደረቦችዎ ለማሳወቅ።
I'm going to have to say no this time.phrase
በዚህኛው ጊዜ አልችልም ማለት አለብኝ።
I've covered a lot of weekend shifts recently, so I'm going to have to say no this time.
ሰሞኑን ብዙ የቅዳሜና እሁድ ፈረቃዎችን ሸፍኛለሁ፤ ስለዚህ በዚህኛው ጊዜ አልችልም ማለት አለብኝ።
ደጋግሞ ለሚጠይቅዎ ሰው በትሕትና ግን በቁርጥ እምቢ ለማለት።
