Skip to content
VocabularyB2 · Upper intermediate

Ending a chat politely

ወሬን በትሕትና መጨረስ

Close a chat in a friendly way without sounding rude.

Printable worksheet

Useful phrases

Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.

  • Well, I won't keep you.phrase

    በል፣ አላቆይህም።

    Well, I won't keep you. Good luck with the exam tomorrow!

    በል፣ አላቆይህም። የነገው ፈተናህ ይቅናህ!

    ሌላው ሰው ሥራ እንዳለበት በማክበር ወሬውን ለመጨረስ።

  • I should let you get back to work.phrase

    ወደ ሥራህ እንድትመለስ ልተውህ።

    Anyway, I should let you get back to work. See you at lunch.

    ለማንኛውም ወደ ሥራሽ እንድትመለሺ ልተውሽ። ምሳ ላይ እንገናኝ።

    በሥራ ቦታ ወሬን በትሕትና ለመጨረስ።

  • It's been great catching up.phrase

    ተገናኝተን በማውራታችን በጣም ደስ ብሎኛል።

    It's been great catching up, Bereket. Let's do it again soon.

    በረከት፣ ተገናኝተን በማውራታችን በጣም ደስ ብሎኛል። በቅርቡ እንደገና እንገናኝ።

    ለረጅም ጊዜ ካላዩት ሰው ጋር ካወሩ በኋላ ለመሰናበት።

  • I'm afraid I have to run.phrase

    ይቅርታ፣ መሄድ አለብኝ።

    I'm afraid I have to run. My class starts at two.

    ይቅርታ፣ መሄድ አለብኝ። ክፍሌ በስምንት ሰዓት ይጀምራል።

    ቸኩለው መሄድ ሲኖርብዎ በትሕትና ለመናገር።

  • Let's stay in touch.phrase

    እንደዋወል፣ አንጠፋፋ።

    Here's my number. Let's stay in touch.

    ቁጥሬ ይኸው። እንደዋወል፣ አንጠፋፋ።

    ከአንድ ሰው ጋር ግንኙነትዎን መቀጠል እንደሚፈልጉ ለመናገር።

Practice· ልምምድ

Question 1 of 6
You are chatting with a neighbour, but your class starts in ten minutes. What do you say?

ከጎረቤትዎ ጋር እያወሩ ነው፤ ክፍልዎ ግን በአሥር ደቂቃ ውስጥ ይጀምራል። ምን ይላሉ?