Asking for time off
ከሥራ ፈቃድ መጠየቅ
Ask your manager for a day off or leave and give a short reason.
Printable worksheetUseful phrases
Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.
Can I take a day off on …?phrase
… ዕለት የአንድ ቀን ፈቃድ መውሰድ እችላለሁ?
Can I take a day off on Friday? My sister is getting married.
ዓርብ የአንድ ቀን ፈቃድ መውሰድ እችላለሁ? እህቴ ልታገባ ነው።
ለአንድ ቀን ከሥራ ለመቅረት ኃላፊዎን ሲጠይቁ።
I need to leave early today.phrase
ዛሬ ቀደም ብዬ መውጣት አለብኝ።
I need to leave early today. I have a doctor's appointment at four.
ዛሬ ቀደም ብዬ መውጣት አለብኝ። አሥር ሰዓት ላይ የሐኪም ቀጠሮ አለኝ።
ከሥራ ሰዓት መጨረሻ በፊት መሄድ ሲያስፈልግዎ።
I have a family emergency.phrase
የቤተሰብ አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞኛል።
Sorry, Ato Yonas. I have a family emergency, so I can't come in today.
ይቅርታ አቶ ዮናስ። የቤተሰብ አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞኛል፤ ስለዚህ ዛሬ ወደ ሥራ መምጣት አልችልም።
ድንገተኛ የቤተሰብ ጉዳይ ገጥሞዎት ከሥራ መቅረት ሲያስፈልግዎ።
I'd like to take my annual leave.phrase
ዓመታዊ ፈቃዴን መውሰድ እፈልጋለሁ።
I'd like to take my annual leave in January to visit my family in Gondar.
ቤተሰቦቼን ጎንደር ለመጠየቅ ጥር ላይ ዓመታዊ ፈቃዴን መውሰድ እፈልጋለሁ።
የዓመት ፈቃድ ለመጠየቅ፤ መደበኛና ትሕትና ያለው አነጋገር ነው።
Is that OK with you?phrase
ለእርስዎ ችግር የለውም?
I'll come back on Tuesday morning. Is that OK with you?
ማክሰኞ ጠዋት እመለሳለሁ። ለእርስዎ ችግር የለውም?
ፈቃድ ከጠየቁ በኋላ ኃላፊዎ መስማማቱን ለማረጋገጥ።
