Skip to content
GrammarB1 · Intermediate

Word order and sentence completion

የቃላት ቅደም ተከተልና ዓረፍተ ነገር ማሟላት

Put words in the right order and choose the correct ending: statements, questions, adverbs, adjectives and indirect questions.

Printable worksheet

How it works

English word order is stricter than Amharic. In Amharic the verb comes at the end; in English it comes straight after the subject.

የእንግሊዝኛ የቃላት ቅደም ተከተል ከአማርኛው ጥብቅ ነው። በአማርኛ ግሱ መጨረሻ ላይ ይመጣል፤ በእንግሊዝኛ ግን ወዲያው ከባለቤቱ በኋላ ይመጣል።

Statements: subject + verb + object + place + time · ዓረፍተ ነገር፦ ባለቤት + ግስ + ተሳቢ + ቦታ + ጊዜ

We met our teacher at the station yesterday.

ትናንት መምህራችንን ጣቢያው ላይ አገኘነው። (አማርኛ፦ ጊዜ … ግስ መጨረሻ)

Adverbs of frequency: before the main verb, after "be" · የድግግሞሽ ተውሳከ ግሶች፦ ከዋናው ግስ በፊት፣ ከ"be" በኋላ

She always drinks coffee. / He is never late.

ሁልጊዜ ቡና ትጠጣለች። / በፍጹም አይዘገይም።

Questions and indirect questions · ጥያቄዎችና ተዘዋዋሪ ጥያቄዎች

Where does he live? → Do you know where he lives?

በተዘዋዋሪ ጥያቄ ውስጥ ቅደም ተከተሉ እንደ ዓረፍተ ነገር ይሆናል (he lives)፤ "does" ይቀራል።

Adjectives: opinion + size + age + colour + noun · ቅጽሎች፦ አስተያየት + መጠን + ዕድሜ + ቀለም + ስም

a beautiful big old white house

የሚያምር ትልቅ አሮጌ ነጭ ቤት

For sentence completion questions, check that the answer joins correctly to the start of the sentence: tense, subject–verb agreement and linking words.

ለዓረፍተ ነገር ማሟያ ጥያቄዎች መልሱ ከዓረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ጋር በትክክል መገናኘቱን ያረጋግጡ፦ ጊዜ፣ የባለቤትና ግስ ስምምነት እና አያያዥ ቃላት።

Examples

Listen, then tap the microphone to record yourself and compare. Your voice stays on your phone.

  1. My brother plays football in the park every Saturday.

    ወንድሜ በየቅዳሜው በመናፈሻው እግር ኳስ ይጫወታል።

  2. We usually have lunch at one o'clock.

    ብዙውን ጊዜ በሰባት ሰዓት ምሳ እንበላለን።

  3. The bus is often late in the rainy season.

    በክረምት አውቶቡሱ ብዙ ጊዜ ይዘገያል።

  4. How long have you lived in Adama?

    በአዳማ ለምን ያህል ጊዜ ኖረሃል?

  5. Could you tell me where the post office is?

    ፖስታ ቤቱ የት እንደሆነ ልትነግረኝ ትችላለህ?

  6. I don't know what time the meeting starts.

    ስብሰባው በስንት ሰዓት እንደሚጀምር አላውቅም።

  7. She bought a lovely long green dress for the wedding.

    ለሠርጉ የሚያምር ረጅም አረንጓዴ ቀሚስ ገዛች።

  8. Although he was tired, he finished his homework.

    ደክሞት የነበረ ቢሆንም የቤት ሥራውን ጨረሰ።

Practice· ልምምድ

Question 1 of 12

Put the words in order

በየጠዋቱ ወተት ትጠጣለች።